አቶ ገዛሄኝ አርስቻ
በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር መሬት አስተዳደርና ኢንቭስትመንት መምሪያ ኃላፊ
መልዕክት
እንደሚታወቀው ኢንቨስትመንት ለከተሞች ዕድገት ከፍተኛ ድርሻ ያበረክታል፡፡ ከተማ አደገ ሲባል ደግሞ ከኢኮኖሚው ባለፈ ማህበራዊ ፋይዳው ብዙ ነው፡፡ በሀዋሳ ከተማ ያለው ወቅታዊ ሁኔታ ከዚህ መሰረታዊ ሀቅ ውጪ አይደለም፡፡ ከተማዋ ለኢንቨስትመንቱ ጠቅማለች፤ ኢንቨስትመንቱ ደግሞ ለከተማዋ ብሎም ደግሞ ለነዋሪዎቿ ብዙ ጠቀሜታዎችን ፈጥሯል፡፡ በከተማችን በተስፋፉ በርካታ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች በስራ ዕድል ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡ይህም ኢንቨስትመንት በከተማው ድህነት ቅነሳ ስራ ላይ አይነተኛ ድርሻ እያበረከተ መኆኑን ያሳየናል፡፡
ይህን ከግምት ውስጥ በማስገባት የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ለዘርፉ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ በመሬት አቅርቦት ብቻ በያዝነው አመት ከ100 ሄክታር መሬት በላይ ለተለያዩ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች አዘጋጅተናል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በዘርፉ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ቀላል፤ ምቹ እና ቀልጣፋ ያደረግን ሲሆን ይህም በተለይ የተገልጋይን እንግልት በማስቀረቱ ረገድ ጉልህ ድርሻ ይኖረዋል፡፡
በአጠቃላይ በከተማችን መጠነ ሰፊ ዝግጅት የተደረገ ሲሆን ይህን ወርቃማ ዕድል እንዲጠቀሙ ስል ለሀገር ውስጥና ለውጪ ሀገራት ባለሀብቶች ጥሪዬን እያቀረብኩ መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንልን እመኛለው፡፡



